Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በምርጫው መገናኛ ብዙኃን የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ መገናኛ ብዙኃን የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ የጋዜጠኝነት ምሁራን ተናግረዋል፡፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የዘርፉ ምሁራን እንደሚሉት በምርጫ ወቅት መገናኛ ብዙኃን ተፎካካሪ ፓርቲዎች ለመራጮች ይዘውት የሚመጡትን ፖሊሲ ያለምንም አድልዎ ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት መምህር ዶክተር ሙላቱ አለማየሁ ሚዲያዎች በምርጫ ሂደት ውስጥ የሚፈጠሩ ሁነቶችን በጥንቃቄ ከመዘገብ ባለፈ ዜጎች የሚወክሏቸውን ፓርቲዎች እንዲመርጡ የሚያስችላቸውን ትክክለኛ መረጃ ማድረስ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
ይህ አላማ ይሳካ ዘንድም መገናኛ ብዙኃን ተፎካካሪ ፓርቲዎችን በአንድ መድረክ በማገናኘት የመወዳዳሪያ ሃሳባቸው እና ፖሊሲያቸውን እንዲያቀርቡ እንዲሁም ፓርቲዎች እርስ በርስ የሚከራከሩባቸውን መድረኮች ማዘጋጀት አለባቸው ነው ያሉት፡፡
እንዲሁም በምርጫ ወቅት መገናኛ ብዙኃን ህብረተሰቡን ወክለው መሞገት እንዳለባቸው በመጥቀስም÷ በተለይም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድን ጨምሮ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማህበራት እና ሌሎች አካላት እየሰሩ ያለውን ስራ ከመጠየቅ ባለፈ ምርመራ ማድረግ አለባቸው ነው ያሉት፡፡
በዚህም ዜጎች ስለ ምርጫው ግንዛቤ እንዲኖራቸው ከማድረግ ባለፈ የምርጫ ውጤቱን አሜን ብለው እንዲቀበሉ የሚያስችል የአዘጋገብ ስልት መከተል እንዳለባቸውም ገልጸዋል፡፡
የሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን መምህር ዕጩ ዶክተር አሰግድ የሽዋስ በበኩላቸው የሚዲያ ተቋማት ምርጫን አስመልክቶ በሚደረጉ ቅስቀሳዎች ወቅት የፖርቲዎችን ሃሳብ በትክክል ከማስተላለፍ ባለፈ የመሞገቻ መድረክ ሆነው ማገልገል እንዳለባቸው ይናገራሉ፡፡
በዚህ ወቅትም ተፎካካሪ ፓርቲዎች ዴሞክራሲን ለማረጋጋጥ ያቀረቡትን አማራጭ፣ ከሃገር ውስጥ አንጻር የያዙትን ፖሊሲ እና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲያቸውን ይዘት በሚመለከት በግልፅ ቋንቋ ለመራጮች ማሳወቅ እንዳለባቸውም ተናግረዋል፡፡
በእርግጥ ግጭት ቀስቃሽ ሃሳቦችን የሚያሰራጩ ፖለቲከኞች አይጠፉም የሚሉት እጩ ዶክተር አሰግድ ይህን ችግር ለመቆጣጠርም መገናኛ ብዙኃኑ የመቆጣጠሪያ ስርዓት ሊኖራቸው እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በመገናኛ ብዙሃን የሚሰራጭ እያንዳንዱ ይዘትም ከፖለቲካ አስተሳሰብ ሳይሆን ከህብረተሰብ ጥቅም፣ ከሀገር ሰላምና ደህንነት እንዲሁም ከብሄራዊ ጥቅም አንፃር መመዘን አለበት ባይ ናቸው፡፡
በመላኩ ገድፍ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳ
የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version