Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ በአቶ ሰንዶካን ደበበ የተመራ ልዑክ ጅግጅጋ ገብቷል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፓሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ በአቶ ሰንዶካን

ደበበ የተመራ ልዑክ ጅግጅጋ ገብቷል።

ኃላፊዎቹ ጅግጅጋ ከተማ ገራድ ዊልዋል አየር ማረፊያ ሲደርሱ የሶማሌ ክልል የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አብዲፈታህ ሼክ ቢሂ አቀባበል አደርገውላቸዋል።

የፌዴራል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከፍተኛ ኃላፊዎች በጅግጅጋ ከተማ ቆይታቸው ቀደም ሲል በክልሉ ለኢንዱስትሪ ፓርኮች በተመደቡ ቦታዎች ላይ ኮርፖሬሽኑ ባጠናው ጥናትና በቀጣይ የኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ግንባታ በሚጀመርበት ሁኔታ ዙሪያ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ መገለጹን ከሶማሌ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version