Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 27 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የገና በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር ለማስቻል ወቅታዊ የከተማዋን የፀጥታ ሁኔታ ያገናዘበ ቅድመ ዝግጅት አድርጎ ወደ ተግባር መግባቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ እንደገለፁት ለበዓሉ በሰላም መከበር በተከናወኑ ቅድመ ዝግጅቶች በተለያዩ አካባቢዎች ከሚገኙ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ከአስተዳደር አካላት፣ ከሃይማኖት ተቋማት፣ ከተለያዩ አደረጃጀቶች እና ከወጣቶች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡
ፖሊስ ኮሚሽኑ የህዝብ እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው ቦታዎች፣ በገበያና በመዝናኛ ስፍራዎች ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም ኮማንደር ፋሲካ ተናግረዋል፡፡
ከበዓላት መቃረብ ጋር ተያይዞ በሚጨምረው የሰዎች እና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ሳቢያ የሚደርሰውን የትራፊክ አደጋ ለመከላከልም ኮሚሽኑ ሙሉ የሰው ሃይሉን ማሰማራቱን ጠቅሰው፥ የበዓሉ ድባብ ከደስታ ወደ ሃዘን እንዳይቀየር አሽከርካሪዎችም ሆኑ እግረኞች ትኩረት አድርገው በሃላፊነት ስሜት ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
እስካሁን ለተገኘው ሰላም የከተማዋ ነዋሪዎች በፀጥታ ጉዳይ ላይ ያደረጉት ንቁ ተሳትፎ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ያስታወሱት ኮማንደር ፋሲካ በዓሉ በሰላም እንዲከበር ፖሊስ ኮሚሽኑ የሚያከናውነውን ተግባር እንደወትሮው በመደገፍ እና አጠራጣሪ ነገሮች ሲጋጥሙም ሆነ መረጃ እና ጥቆማ መስጠት እንዲተባበሩም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ጥቆማ ለመስጠትም በየአቅራቢያቸው በሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች በግንባር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥሮች 011-1-11-01-11 እና በ991 በመደወል የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪ አቅርቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳ
የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version