Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቦረና ዞን ድሬ ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ የሰባት ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ድሬ ወረዳ በዛሬው ዕለት በደረሰ የመኪና አደጋ የሰባት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡

አደጋው የደረሰው ወደ ዲሎ ገበያ ሰዎችን አሳፍሮ በመጓዝ ላይ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ መኪና በመገልበጡ ነው፡፡

በዚህም የሰባት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በርካታ ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል ጉዳት መድረሱን ከድሬ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Exit mobile version