አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ
የሚገነባው የካሊድ ዲጆ መስኖ የልማት ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረ።
የሚገነባው የካሊድ ዲጆ መስኖ የልማት ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረ።
ፕሮጀክቱን የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው ፣የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ እና የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈርያት ካሚል በይፋ አስጀምረውታል።
ግድቡ 27 ሜትር ከፍታና 1 ሺህ 731 ሜትር ርዝመት ሲኖረው 8 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃ የመያዝ አቅም ይኖረዋል ነው የተባለው።
ፕሮጀክቱ በ1 ነጥብ 19 ቢሊየን ብር በጀት የሚገነባ ሲሆን በ2 ዓመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ታውቋል፡፡
የግድቡ ስራ ሲጠናቀቅም 1 ሺህ 800 ሄክታር መሬት የማልማት አቅም ያለው ሲሆን 7 ሺህ 200 አባወራና እማወራዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል።
የአከባቢው ነዋሪዎች ወንዞቹ ከዚህ ቀደም ያለጥቅም ሲፈሱ መቆታቸውን ተናግረው አሁን ግን የመስኖና ግድብ ፕሮጀክቶቹ ተስፋ እንደሰጣቸው ገልፀዋል።
ግንባታውን የሚያካሂደው ሀገር በቀሉ የደቡብ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን በተያዘለት የሁለት አመት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን ገልጿል።
በዘመን በየነ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

