አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርት ሚኒስቴር ላለፈው አንድ አመት ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ በሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ ጥናት አደረገ፡፡
ጥናቱ ኢፕቲሳ ከተባለ ዓለም አቀፍ የስፔን ኩባንያ ጋር በቅንጅት የተካሄደ ነው ተብሏል፡፡
በሀገሪቷ በሚገኙ አምስት ክልሎች ላይ ጥናት ሲደረግ 2 ሺህ ኪሎ ሜትርም በናሙናነት ተወስዷል ነው የተባለው፡፡
በጥናቱ መሰረትም መንገዶቹ በራሳቸው ለትራፊክ አደጋ አጋላጭ መሆናቸው ተነግሯል፡፡
የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ጥናቱ መደረጉ ለአሁኑ ብቻ ሳይሆን ቀጣይ ለሚሰሩ መንገዶችም ትምህርት የተገኘበተ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በፈቲያ አብደላ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

