አዲስ አበባ ፣ጥር 4 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተገልጋይን እርካታ የሚጨምሩና ለኦዲት ምቹ የሆኑ የፋርማሲ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ጤና ተቋማት ተመረቁ።
በሲዳማ ክልል ለኦዲት ምቹ የሆነ የፋርማሲ አገልግሎት ለመስጠት ብቁ የሆኑ 12 ተቋማት ተመርቀው ስራ ጀምረዋል፡፡
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ ተቋማቱን መርቀው ስራ ባስጀመሩበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ÷ የፋርማሲ አገልግሎትን የማሻሻል ኢንሺዬቲቭ በጤና ሴክተር የአገልግሎት ጥራትን ለማረጋገጥ ከተጀመሩ ስራዎች አንዱ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህም የግልጸኝነትና የተጠያቂነት ስርዓትን እንደሚያጠናክር ገልጸው÷ ቁርጠኝነት ካለ በሁሉም ተቋማት ለመተግበር ይቻላል ብለዋል።
የጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ዮሐንስ ያታሞ በበኩላቸው÷ በበጀት ዓመቱ ተጨማሪ 3 ተቋማት ወደ ስራ እንደሚገቡ የገለፁ ሲሆን ጤና ሚኒስቴር 190 የፋርማሲ ባለሙያዎችን በማሰልጠን ሙያዊና የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ላሳየው ድጋፍ አመስግነዋል።
ለቀጣይ ውጤታማነም የመድኃኒት አቅርቦት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ ጠቁመዋል።
ጤና ሚኒስቴር በ2013 በጀት ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ የ80 ጤና ተቋማትን የፋርማሲ አገልግሎትን ጥራት በማሻሻል የተገልጋዮችን እንግልት በመቀነስ እርካታ ለመጨመር እንዲሁም ግልፀኝነትና ተጠያቂነትን ያሰፈነ ለኦዲት ምቹ የፋርማሲ አገልግሎት ለማስጀመር እየሰራ መሆኑ ተመላክቷል።
በዚህም 54 ጤና ተቋማት የሚጠበቅባቸውን መስፈርት አሟልተው አገልግሎት መጀመራቸውን ከእነዚህም መካከል 12ቱ በሲዳማ ክልል እንደሚገኙ ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

