Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሶማሌ ክልል ም/ር መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ የሀገር ሽማግሌዎች በክልላዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) እየተተገበረ ባለው የህግ ማስከበር ስራ የሀገር ሽማግሌዎች የበኩላቸውን እንዲወጡ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀሙድ ጥሪ አቀረቡ።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ በወቅታዊ ክልላዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን የሶማሌ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሸን አስታውቋል።

በውይይቱም በክልሉ የሰፈነውን ሰላም የበለጠ ለማጠንከር እና በሀገሪቱ እየተተገበረ ባለው የህግ ማስከበር ስራዎች የሀገር ሽማግሌዎች የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version