አዲስ አበባ ፣ ጥር 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የወጣቶች የብሄራዊ በጎፈቃድ አገልግሎት ስልጠና በአርሲ ዩኒቨርስቲ እየተሰጠ ነው።
ስልጠናው ለ45 ቀናት የሚሰጥ ሲሆን ከመላ ኢትዮጵያ የተወጣጡ የዩቨርስቲና የኮሌጅ ምሩቃን ይሳተፉበታል።
ስልጠናው በተግባር ልምምድና በንድፈ ሀሳብ ትምህርቶች እንደሚሰጥም ተገልጿል።
ስልጠናው የወጣቶችን ውጤታማነትና በገቢያ ተፈላጊነት ማሳደግን ማቀዱ ተገልጿል።
በዚህ ወቅት በቪዲዮ የቀጥታ መልዕክት ያስተላለፉት የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል÷ ስልጠናው የወጣቶችን ብቃትና ክህሎት በማሳደግ ለሀገር የበኩላቸውን እንዲወጡ ማስቻልን ያለመ ነው ብለዋል።
ስልጠናው ከየትኛውም የፖለቲካ ርዕዮት ነፃ የሆነ መሆኑን የገለፁት ወይዘሮ ሙፈሪያት÷ ትውልድን የመገንባትና የማነፅ አላማ እንዳለውም አስረድተዋል።
በስልጠናው ወቅት የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች፣ የብሔራዊ መግባባትና የሀገር ፍቅር ግንባታ፣ የባህል ትውውቅና ልውውጥ፣ የተዛነፉ የታሪክ ነገራ መንገዶችን ማረም፣ የተመራቂዎችን የስራ ፈጠራ ክህሎትን ማሳደግ ትኩረት ይሰጥባቸዋል ብለዋል።
“የማይተዋወቅ ሰው ሊከባበርና ሊዋደድ አይችልም” ያሉት ሚኒስትሯ ወጣቶችን የማቀራረብ ውጥን መኖሩንም አስረድተዋል።
መሰል ስልጠናዎች በየደረጃው ወደፊትም ይሰጣሉ ተብሏል።
ስልጠናውን ወስደው የሚያጠናቅቁ እውቅና የሚሰጣቸው ሲሆን÷ ያገኙትን እውቀት ለሀገራቸው እንዲያውሉም ይጠበቃል።
በአፈወርቅ እያዩ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share

