Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ያስገነባቸውን ሁለት የሁለተኛ ደረጃ ት/ት ቤቶች አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ያስገነባቸውን ሁለት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አስመረቀ፡፡
በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ ቀዳማዊትእመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ፣ የጎሳ መሪዎች እና አመራሮች ተገኝተዋል::
በጅግጅጋ ከተማ የተገነቡት ጅግጅጋ እሌይስ አንድ እና ጅግጅጋ እሌይስ ሁለት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እያንዳንዳቸው በ13 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የተገነቡ ሲሆን የ ቤቶቹ ስያሜም በሶማልኛ ቋንቋ ብርሃን ማለት ነው ተብሏል፡፡
ትምህርት ቤቶቹ በውስጣቸው የአስተዳደር ህንጻ፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ የቤተ መጽሀፍት፣ የስብሰባ አዳራሽ እና የመጸዳጃ ህንጻዎችን አካተዋል፡፡
በሙሉ አቅማችው መቀበል ሲጀምሩም እያንዳንዳቸው በሁለት ፈረቃ 1 ሺህ 800 ተማሪዎችን የመቀበል አቅም አላቸው ነው የተባለው፡፡
በትምህርት ቤት እርቀትና እጥረት ምክንያት ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ገበታ ላላኩ የአካባቢው ነዋሪዎች እና ለአዋሳኝ ቀበሌ ነዋሪዎች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት በመላክ እድሉን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል::
ጽህፈት ቤቱ በዛሬው እለት ያስመረቃችውን ጨምሮ እንደ ሃገር ግንባታችው ተጠናቆ ያስመረቃቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቁጥር ዘጠኝ የደረሰ ሲሆን ቀሪዎቹን በቅርብ ቀን በሁሉም ክልሎች እንደሚያስመርቅ ተገልጿል፡፡
ትምህርት ተደራሽ ባልሆነባቸው ሌሎች አካባቢዎችም የትምህርት ቤት ግንባታው በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚጀመር ነው የተገለጸው፡፡
ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ትምርት ቤቶቹን መርቀው ለመክፈት ዛሬ ረፋድ ጅግጅጋ ከተማ መግባታቸው ይታወቃል፡፡
በፍሬህይወት ሰፊው
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version