Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በገጠራማው የኢትዮጵያ ክፍል ለሚኖሩ ዜጎች ዘመናዊ የሃይል ምንጮችና ቴክኖሎጂዎችን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሠራ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በገጠራማው የኢትዮጵያ ክፍል ለሚኖሩ ዜጎች ዘመናዊ የኢነርጂ ምንጮችንና ቴክኖሎጂዎችን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሠራ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ተናገሩ፡፡
በኢትዮጵያ 80 በመቶ ከሚሆነውና በግብርና ከሚተዳደረው የህብረተሰብ ክፍል በአብዛኛው የኤሌክትሪክ ኃይል የማያገኝ በመሆኑ ለምግብ ማብሰያና ለመብራት የማገዶ እንጨትን፣ የከብቶችን ፍግና ከሰልን እንደሚጠቀም ገልጸዋል፡፡
ይህን ለመቀየርም ዘመናዊ የሃይል ምንጮችና ቴክኖሎጂዎችን ተደራሽ ለማድረግ በማዕከሉ በኩል እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ የገጠር ኢነርጂ ልማት ማስፋፊያ ማዕከል በአዋጅ 269/1994 ዓ.ም ተቋቁሞ በገጠር አካባቢ ያለውን የኢነርጂ አቅርቦት እያጠና የሃይል ምንጮችን በማልማትና በማስፋፋት በርካታ ሥራዎችን ሲሠራ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
ከዚያም በአዋጅ 691/2003 ማዕከሉ ፈርሶ ስልጣንና ተግባሩ ለውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ ለአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን እና ለማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ተሰጥቶ ቆይቶ ነገር ግን በአዋጅ 1097/2011 ዓ.ም እንደገና ተቋቁሞና የመዋቅር ጥናት ተካሂዶ በድጋሚ ተደራጅቶ ሥራውን በይፋ ጀምሯል፡፡
የኢትዮጵያ ገጠር ኢነርጂ ልማት ማስፋፊያ ማዕከልም የተሻሻሉ ማገዶ ቆጣቢ የማብሰያ ምድጃዎች፣ የባዮ ጋዝ ቴክኖሎጂ፣ የሶላር ሆም ቴክኖሎጂ፣ አነስተኛ ኃይድሮ ፖወርና የባዮ ፊውል ቴክኖሎጂዎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ ከውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version