አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና ለተጠሪ ተቋማት ሴት አመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች በቢሾፍቱ ከተማ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡
ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የሰላም ሚኒስቴር የማኔጅመንት ድጋፍ ሥራ አመራር ዳይሬክተር ጀነራል አቶ መብራቱ ካሳ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱንና የተጠሪ ተቋማትን የጋራ ራዕይ እና ተልዕኮ ለማሳካት የሴት አመራሮችንና ባለሙያዎችን አቅም ማጎልበት ወሳኝነት አለው ብለዋል፡፡
መንግስት የሚያወጣቸውን ፖሊሲዎችና አዋጆች የሴቶችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ያካተተ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋልም ነው ያሉት፡፡
አያይዘውም የሀገሪቱን ዘላቂ ሰላም እና ሁለንተናዊ ዕድገት ለማፋጠን ሴት አመራሮችንና ባለሙያዎችን በተሰማሩበት የስራ መስኮች ኃላፊነታቸውን በብቃት እንዲወጡ ዕገዛ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል፡፡
በስልጠናው ላይ የሰላም ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት የሴቶች የጋራ ፎረም መተዳደሪያ ደንብ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

