Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስተሪ ፓርክን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በይርጋለም የተቀናጀ የግብር ማቀነባበሪ ኢንዱስተሪ ፓርክን በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል።

በጉብኝቱ ላይ ሲዳማክ ክልል ርዕሰ መስተዳር አቶ ደስታ ሌዳሞ ፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ኔሜ፣ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዳንኤል ቴሬሳ እና የፓርኩ አስተዳደር ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ለጉብኝቱ በኋላ የኮሚሽኑ የስራ ሃላፊዎች ፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እና የተቀናጀ የግብርና  ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የስራ ሃላፊዎች በኢንቨስትመንት አማራጮች እና የስራ ፍሰትን በተመለከተ ውይይት አድርገዋል።

እንዲሁም ከማስታወቂያ ፣ ሰራተኞች ፣ ደህንነት እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮ ሃር በተያያዘ በጋራ ለመስራት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version