Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከፊንላንድ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከፊንላንድ ፕሬዚዳንት ሳኡሊ ኒኒስቶ ጋር በስልክ ተወያዩ።
የኢትዮጵያና የፊንላንድን ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ በስልክ መክረዋል።
ፕሬዚዳንት ኒኒስቶ የትግራይ ክልልና በአፍሪካ ቀንድ ስላለው ሁኔታ ለመረዳት ስልክ እንደደወሉላቸው ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገልጸዋል።
የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ያመለክታል።
የፊንላንድ ፕሬዚዳንት ኒኒስቶ ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያን መጎብኘታቸውን ፕዚዳንቷ አስታውሰዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version