አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) አንዳችን ለሌላችን ዘብ በመቆም ፤እየተደጋገፍን የፍቅራችንን መልካም መዓዛ ለተከታይ ትውልድ ማስረከብ ይጠበቅብናል አሉ የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው።
ሚኒስትሯ በጃን ሜዳ በተከበረው የጥምቀት በዓል ላይ ተገኝተው ለእምነቱ ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዶ/ር ሂሩት በመልዕክታቸው ዛሬ በታላቅ ድምቀት የምናከብረው የጥምቀት በዓል በዓለም ቅርስነት በተመዘገበበት ወቅት ነው ብለዋል።
ጥምቀትን ጨምሮ በሀገራችን የሚከበሩ ባህላዊም ሆነ ሀይማኖታዊ በዓላት በሚከበሩበት ወቅት በጋራ እና በመገዳገፍ የማክበር ባህላዊ እሴቶች መኖራቸውን አስታውሰዋል።
ፍቅርን አስቀድመን ፤አንዳችን ለሌላችን ዘብ በመቆም ፤እየተደጋገፍን የፍቅራችንን መልካም መዓዛ ለተከታይ ትውልድ ማስረከብ ይጠበቅብናልም ብለዋል።
ሚኒስትሯ ሁሉም ለሰላም እና ለፍቅር ጥብቅና እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

