አዲስ አበባ ፣ ጥር 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል የበረሃ አንበጣ ዳግም መከሰቱን የክልሉ እርሻ፣ አርብቶ አደርና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።
በቢሮው የበረሃ አንበጣ መከላከል ግብረ-ሃይል አስተባባሪ ዶክተር አያሌው ሹመት ለኢዜአ እንደገለጹት በክልሉ አፋምቦ፣ ዱብቲና አይሳኢታ ወረዳዎች ጥር 9 ቀን 2013 ዓ.ም የአንበጣ መንጋው ዳግም ተከስቷል።
መነሻውን ከጅቡቲና ሶማሌ ያደረገው የአንበጣ መንጋ በሌሎችም የክልሉ ወረዳዎች እየተስፋፋ መሆኑን ተናግረዋል።
በክልሉ ሚሌ፣ ጭፍራ፣ ጉሊና እና ቴሩ ወረዳዎች የአንበጣ መንጋው የተስፋፋባቸው መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።
አሁን ላይ በክልሉ የግብርና ስራዎች የሚከናወኑበት ወቅት በመሆኑ የአንበጣ መንጋው ከእንስሳት መኖ በተጨማሪ በሰብል ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ህብረተሰቡን በማሳተፍ በባህላዊ መንገድ የመከላከል ስራ እየተካሄደ ነው ብለዋል፡፡
መንጋውን ለመቆጣጠር በሰውና በተሽከርካሪ ኬሚካል ለመርጨት አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር በአውሮፕላን የታገዘ ርጭት ለማካሄድ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

