Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአምባሳደር ድንበሩ ዓለሙ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የአምባሳደር ድንበሩ ዓለሙ የቀብር ስነ ስርዓት በኮልፌ የሙስሊም መቃብር ተፈፅሟል።
የአምባሳደር ድንበሩ ዓለሙ የቀብር ስነ ስርአት የተፈጸመው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንና እና ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች በተገኙበት ነው።
አምባሳደር ድንበሩ ዓለሙ በዱባይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት በዲፕሎማትነት በማገልግል ላይ እያሉ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ጥር 09 ቀን 2013 ዓ.ም ሕይወታቸው ማለፉ የሚታወስ ነው ።
Exit mobile version