አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ ኤጀንሲ 3 ሚሊየን 96 ሺህ 657 ብር ዋጋ ያላቸውን ህይወት አድን መድሀኒቶች ወደ ሽረ እያጓጓዘ መሆኑን አስታወቀ።
ከጥር 12 ቀን 2013 ጀምሮ ህይወት አድን መድሐኒቶቹን እያጓጓዘ መሆኑን ነው ኤጀንሲው የገለፀው።
በዋናነት ለእናቶች እና ህፃናት የሚውለውን ህይወት አድን መድሀኒቶች፣ የህክምና ግብዓቶች፣ ለፀረ ወባ፣ ሳንባ ነቀርሳ እና ኤች አይ ቪ ኤድስን ለማከም የሚረዱ መድሀኒቶች ናቸው እየተጓጓዙ የሚገኙት።
ለሎችም እንደ Tetanus Antitoxin, propyithiouracil tablet, pethidine HCL Ampoule, hydrocortisone sodium succinct, Insulin isophane, soluble and biphasic የመሳሰሉ መድሃሐኒቶች እንደሚገኙበት ተነግሯል፡፡
መድሀኒቶች እና የህክምና ግብዓቶቹ ሽረ ቅርንጫፍ ሲደርሱ ለጤና ተቋምት እንደሚከፋፈሉ ከኤጀንሲው የተገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

