Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የበጎ ፈቃደኞች ተግባር የአሁኑ ትውልድ ቅርስ ሆኖ የሚያገለግል ነው – ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ እየሰለጠኑ ካሉ በጎ ፈቃደኛኞች ጋር ተወያዩ።

በኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል የተመራ ልዑክ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ እየሰለጠኑ ያሉ 471 በጎ ፈቃደኛኞችን ጎብኝተዋል።

ወ/ሮ ሙፈሪያት የበጎ ፈቃደኞቹን ቁርጠኝነት አድንቀው የበጎ ፈቃደኞቹ ተግባር የአሁኑ ትውልድ ቅርስ ሆኖ ሊያገለግል እንደሚችል መግለጻቸውን ከጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version