Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በምርጫ ቦርድ ረቂቅ መመሪያዎች ላይ ውይይት አካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምርጫ ቦርድ ረቂቅ መመሪያዎች ላይ ከጤና ባለሙያዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የፀጥታ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል።
በዚህም ከምርጫ ቅስቀሳ ጀምሮ በሚኖሩ የምርጫ ሒደቶች፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሊያስከትል የሚችለውን ጫና መቀነስ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መመሪያ ተዘጋጅቶ ውይይት ተደርጎበታል።
መመሪያ ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ማለትም እድሜያቸው ከ60 በላይ የሆኑ ሰዎች፣ ነፍሰጡር ሴቶችና የአካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
በተጨማሪም የአስም፣ የስኳርና የደም ግፊት በሽታ ያለባቸው ወይም የሃኪም ማስረጃ ያላቸው እንዲሁም በሽታ የመከላከል አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑ ሰዎችን የሚያካትት ነው፡፡
በምርጫ ወቅት ከአባልነት ምዝገባ እስከ ድጋፍ ማሰባሰብ እንዲሁም ህዝባዊ ስብሰባዎች እና እንቅስቃሴዎች ጨምሮ በምርጫ ድምፅ ቆጠራ የምርጫ ታዛቢዎች ርቀታቸውን ጠብቀው ይታዘባሉ የሚለውን ጨምሮ ረቂቁ የህዝባዊ ስብሰባዎችን እና እንቅስቃሴዎች የሚደረጉበትን ቦታዎች የሚከለከሉ መመሪያዎችን አውጥቷል፡፡
ከእነዚህ ቦታዎች ውስጥም የመንግስት ሆስፒታሎች፣ የኮሮና ቫይረስ ህክምና መስጫ እና ለይቶ ማቆያ ማዕከሎች፣ የአረጋውያን ማቆያ ማዕከሎች የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ አይቻልም ተብሏል፡፡
ይህም የሆነው እነዚህ ስፍራዎች የኮሮና ቫይረስ ስጋት ያለባቸው ቦታዎች በመሆናቸው ነው ተብሏል፡፡
በተጨማሪም የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል የማያደርጉ የምርጫ አስፈፃሚዎች፣ የቦርዱ ሰራተኞች፣ እጩዎች፣ የፓርቲ ወኪሎች እና ጋዜጠኞች ወደ ቦርዱ ግቢ እና የቅሬታ ማስፈፀሚያ እንዳይገቡ ይደረጋል የሚል የቅጣት መመሪያንም ያካትታል ረቂቁ፡፡
በፀጋዬ ንጉስ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version