Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በትግራይ ክልል ህግ በማስከበሩ ሂደት ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በትግራይ ክልል ህግ በማስከበሩ ሂደት ለተጎዱ ዜጎች ከ18 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ፡፡
አስተዳደሩ ህግ በማስከበር ሂደቱ ለተጎዱ ዜጎች ያደረገው ድጋፍ 2 ሺህ ኩንታል ጤፍ፣ 2 ሺህ ኩንታል ስንዴና 2 ሺህ ኩንታል በቆሎ መሆኑ ታውቋል፡፡
ይህም በገንዘብ ሲሰላ 18 ሚሊየን 340 ሺህ ሲሆን፥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ለትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ዶክተር አብርሃም በላይ አስረክበዋል፡፡
በዚህ ወቅት ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ድጋፉ የመጀመሪያ ዙር መሆኑንና ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
ዶክተር አብርሃም በላይ በበኩላቸው ለድጋፉ አመስግነው ድጋፉ በአግባቡ ለተጎጂዎች እንደሚደርስ ገልፀዋል፡፡
በትዝታ ደሳለኝ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version