Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የደራሼ ባህል ፌስቲቫል በጊዶሌ ከተማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የደራሼ ህዝብ ባህላዊ እሴቶች ተጠብቀው እንዲቆዩ የሚያግዝ የባህል ፌስቲቫል በጊዶሌ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በፌስቲቫሉ በአካባቢው ባህላዊና ታሪካዊ ሀብቶች ዙሪያ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ተገልጿል።

የደራሼ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳደሪ አቶ አመኑ ቦጋለ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የደራሼ ብሄረሰብ ባህላዊ እሴቶች ሳይበረዙ ለትውልድ እንዲተላለፉ ለማስቻል እየተሰራ ነው።

ወጣቱ ባህላዊ እሴቶቹን አውቆ እንዲጠብቅ ለማገዝ ፌስቲቫሉ መዘጋጀቱን ገልጸው፤ የአብሮነት፣ አንድነትና ትብብር ተምሳሌት የሆኑ እሴቶች የብሄረሰቡ መገለጫዎች እንደሆኑ ጠቁመዋል።

የደራሼ ብሄረሰብ ያለውን በጋራ ተረዳድቶና ተጋግዞ የመኖር ልምድ እንዲያጎለብት ፌስቲቫሉ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።

ለሶስት ቀናት በሚቆየው ፌስቲቫል በልዩ ወረዳው የሚገኙ የደራሼ፣ ኩስሜ፣ ሞስዬና ማሾሌ ብሔረሰቦች ባህላዊ እሴቶች እንደሚተዋወቁና ጉብኝት እንደሚካሄድ ለማወቅ ተችሏል።

በፌስቲቫሉ ሥነ-ሥርዓት ከልዩ ወረዳው ሌላ ከፌደራል እና ደቡብ ክልል የተውጣጡ የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ሴክተር ባለሙያዎችና ተጋባዥ እንግዶች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version