አዲስ አበባ ፣ ጥር 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በቻይና ቾንግኪንግ በተካሄደው የሙያ ትምህርት ጥምረት የመክፈቻ ሥነ ስርዓት ተሳትፋለች፡፡
በስነስርዓቱ ላይ በቾንግኪንግ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት፣ የትምህርት ሚኒስቴር፣ ጄኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና የሆለታ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡
ጥምረቱ ከአፍሪካ ሃገራት ጋር በመስራት በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ላይ የቻይናን ተሞክሮ ለመተግበር ያለመ ነው ተብሏል፡፡
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ወቅት በቾንግኪንግ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል አቶ አንተነህ ታሪኩ እንደተናገሩት የሕብረቱ መጀመር ለአፍሪካ ወቅታዊ ፍላጎት ትክክለኛ ምላሽ ነው ፡፡
በመድረኩ በቴክኒክና ሙያ መስክ የሰለጠነ የሰው ሃይል የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለመገንባት አስፈላጊ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
ጥምረቱ ቀደም ሲል በአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያን፣ ዑጋንዳ ፣ ኬንያ እና ታንዛኒያን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት ፕሮጀክቶች ያሉት ሲሆን በአሁኑ ወቅት በዓለም ባንክ የሚደገፉ 7 ዋና ዋና ፕሮጀክቶች በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች አሉት ፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

