አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል በልዩ ልዩ ምክንያቶች ቷቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለማስጀመር እየተሰራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮችና ባለሙዎች በትግራይ ክልል በቀጣይ ትምህርት ለማስጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከክልሉ ጊዜያዊ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር መክረዋል፡፡
ለናሙናነት በተካሄዱ የመስክ ምልከታዎች እንደተረጋገጠው በክልሉ የሚገኙ የትምህርት መሠረተ-ልማትና ግብዓቶች በህወሃት የጥፋት ቡድን ጉዳት እንደደረሰባቸውና እንደተዘረፉ ለማወቅ ተችሏል ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡
የመማር-ማስተማር ሥራው በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ ነበረበት እንዲመለስ የክልሉ መንግሥትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚያደርጉትን ጥረት ለማገዝ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቀጣይነት ያለው ድጋፍና ክትትል የሚያደርግ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ሁሪያ አሊ አረጋግጠዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

