Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሁሉን አቀፍ ሀገራዊ ምክክር ለማድረግ ዝግጅት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ማይንድ ኢትዮጵያ የተባለ የሰባት ተቋማት ስብስብ በኢትዮጵያ ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር ሁሉን አቀፍ ሀገራዊ ምክክር ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል።

የማይንድ ኢትዮጵያ አባልና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የቀድሞ ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ 38 የፖለቲካ ፓርቲዎች የምክክር መድረኩ እውን እንዲሆን ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
አላማው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ወደ መግባባት እንዲመጡና ለአንድ አላማ እንዲሰሩ ማድረግ መሆኑንም ተናግረዋል።

በቀጣይ ለሚደረገው ሀገራዊ ምክክርም የውይይት አጀንዳዎችን፣ አወያዮችን፣ የጥናት ጽሁፎችን እና ጥናት አቅራቢዎችን የመለየት ስራ እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል።

የዴስቲኒ ኢትዮጵያ ኃላፊ አቶ ንጉሱ አክሊሉ በበኩላቸው በተደረገው ጥናት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ሀገራዊ መግባባት እንዲኖር የሚፈልጉ በመሆኑ በቅርቡ ሀገራዊ ምክክር ለማድረግ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።

በዘመን በየነ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version