አዲስ አበባ፣ ጥር 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀጣዩ ምርጫ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ ተገኝተው በምርጫ የመወዳደሪያ ምልክታቸውን አንዲወስዱ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጥሪ አቀረበ።
የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ምልክት መረጣ ትናንት የተጀመረ ሲሆን እስከ ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።
እስካሁን ህጋዊ ምዝገባቸውን ካጠናቀቁ 53 የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል 25ቱ የምርጫ ምልክት ለመውሰድ በመጀመሪያው ቀን ምርጫ ቦርድ መገኘታቸው ተገልጿል።
ለዕጩዎች አማራጭ የመወዳደሪያ ምልክቶችን ያቀረበው ምርጫ ቦርድ የፓርቲ ተወካዮች ከተዘጋጁት ምልክቶች ሊወክለኝ ይችላል የሚሉትን መምረጥ ይችላሉ ብሏል።
ይወክለኛል የሚሉትን ምልክት ከምርጫ ቦርድ ካጡ የራሳቸውን አማራጭ ማቅረብ እንደሚችሉም አስቀድሞ ተገልጿል።
በአልዓዛር ታደለ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

