Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ እርስቱ ይርዳ በጎፋ ዞን ጉብኝት እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ በጎፋ ዞን ኡባ ደብረ ፀሀይ ወረዳ የበቶ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን የግንባታ ሂደት ጎበኙ፡፡

የበቶ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2008 ዓ.ም በ25 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግንባታው የተጀመረ ሲሆን፥ ሆስፒታሉ እስካሁን ድረስ ባለመጠናቀቁ ለህብረተሰቡ የቅሬታ ምንጭ ሆኖ ቆይቷል፡፡

አቶ እርስቱ ይርዳ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት በክልሉ በተለያዩ ምክንያቶች የተጓተቱ ፕሮጀክቶችን ወደ ስራ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ ነው፡፡

የበቶ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን የግንባታ ሂደት በፍጥነት ወደ ስራ በማስገባት ለማጠናቀቅ የክልሉ መንግሥት ልዩ ትኩረት ይሰጣል ብለዋል፡፡

የሆስፒታሉ ግንባታ ሲጀመር የአካባቢውን ህብረተሰብ የጤና ተደራሽነት ችግር ይቀርፋል የሚል እምነት እንደነበራቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

መንግሥት የሆስፒታሉን የግንባታ ሂደት መጓተት ችግር በማጥናት አፋጣኝ መፍትሄ ሊሰጠው ይገባልም ብለዋል፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በጎፋ ዞን ቆይታቸው ልዩ ልዩ ልዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ይጎበኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version