Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሁሉም ዘርፎች እንዲያድጉ ከተፈለገ ለትራንስፖርት ዘርፉ መዘመን ትኩረት ሊሰጥ ይገባል-አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ ፣ ጥር 18 ፣ 2013  (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሁሉም ዘርፎች እንዲያድጉ ከተፈለገ ለትራንስፖርት ዘርፉ መዘመን ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ይህንን ያሉት በትራንስፖርት ዘርፉ የ10 ዓመት መሪ የልማት እቅድ ዙሪያ ውይይት እየተካሄደ ባለበት መድረክ ነው።

አቶ ደመቀ በተለይ በኢትዮጵያ ያለውን የአግሮ ኢኮኖሚ፣የቱሪዝም እና ሌሎች የኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፎች ውጤታማ ለማድረግ የትራንስፖርት ዘርፉን ማዘመን ይገባል ብለዋል ።

ለ10 ዓመት የልማት ዕቅዱ ትግበራ እና ውጤታማነትም  ከፌደራል እስከ ክልል ያሉ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትኩረት መስራት ይኖርባቸዋልም ተብሏል።

አቶ ደመቀ በሚቀጥሉት 10 የኢትዮጵያ ብልጽግና አፍሪካዊ ተምሳሌት እንድትሆን ለማስቻል መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል  ሲሉም ገልጸዋል።

ወቅታዊ ፈተናዎችን በብልሃት ለመሻገር አንድነትት ማጠናከር ይገባልም ብለዋል አቶ ደመቀ መኮንን።

አቶ ደመቀ መኮንን አያይዘውም ኢትዮጵያዊ አንድነትን በማጠናከር የታፈረች እና የተከበረች ሃገርን እውን ማድረግ ይቻላል ነው ያሉት።

በውይይት መድረኩ ሚኒስትሮች የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው።

በምስክር ስናፍቅ

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version