Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሀዋሳ ከተማ ያላትን የተፈጥሮ ፀጋ በመጠቀም የነዋሪዎቿን ህይወት ለመለወጥ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ትልቅ ተስፋን የሚያሳድሩ ናቸው- ኢንጂነር አይሻ መሃመድ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 18 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ በሀዋሳ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ጎበኙ፡፡
ሚኒስትሯ በሀዋሳ ከተማ እየተገነባ ያለውን የሁለት ኪሎ ሜትር የጎርፍ ማስወገጃ፣በሀዋሳ እየተከናወኑ ያሉ የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን እንዲሁም በደብረ ታቦር ተራራ ዙሪያ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ነው የጎበኙት።
በጉብኝቱ ሀዋሳ ከተማ ሰላም ሙሉ በሙሉ መመለሷንና ወደልማት መግባቷን ለመገንዘብ ችያለሁ ያሉት ሚኒስትሯ ይህም ለሌሎች ከተሞች ትልቅ አርአያ ነው ብለዋል።
ሀዋሳ ያላትን የተፈጥሮ ፀጋ በመጠቀም የነዋሪዎቿን ህይወት ለመለወጥ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችም ትልቅ ተስፋን የሚያሳድሩ ናቸው ያሉት ኢንጂነር አይሻ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ለወጣቶች የስራ ዕድሎችን በማስገኘት በኩል የፈጠሩት ዕድል ማደግ ይኖርበታልም ሲሉ ገልፀዋል።
የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ፕሮፌሰር ፀጋዬ ምትኩ በበኩላቸው ከተማዋ በተለይም ለወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥሩ በርካታ ፕሮጀክቶችን ይፋ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።
እስካሁንም ከ13 ሺህ በላይ ወጣቶች ወደስራ መግባታቸውን ተናግረው በቅርቡም በርካታ ወጣቶችን ወደስራ እናሰማራለን ማለታቸውን ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version