አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአስር አመት ታዳጊ የሆነችው ኢትዮጵያዊቷ ሶልያና ግዛው አፍሪካን ኮድ (AfriCANCode) በተሰኘው ውድድር የ2020 አሸናፊ ሆናለች፡፡
ሶልያና በዚህ ውድድር አሸናፊ የሆነችበት ማትስቴይንመንት (Mathstainement) የተሰኘ ፕሮጀክት መሆኑን አፍሪካ ኮድ ዊክ ዘግቧል፡፡
ይህ ፕሮጀክት የሞባይል መተግበሪያ ሲሆን መሰረታዊ የሒሳብ እውቀቶች ቀላል፣ መካከለኛና ከባድ በሚል ደረጃ የከፈለና ታዳጊዎች እየተዝናኑ የሒሳብ ዕውቀት የሚገበዩበት ብቻ ሳይሆን ስለ ኮሮና ቫይረስ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ መሆኑ ልዩ ያደረገውና ለአሸናፊነት ያበቃት መሆኑ ታውቋል፡፡
በዚህ ኢትዮጵያዊቷ ታዳጊ ሶልያና አሸናፊ በሆነችበት ውድድር የመጀመሪያዎቹ 10 ተወዳዳሪዎችና ሀገሮች ይፋ የተደረጉ ሲሆን÷ ሶልያያናን ተከትለው የደቡብ አፍሪካና የአልጄርያ ታዳጊዎች የሁለተኛና የሶስተኛን ደረጃ መያዛቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

