Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ እና ኢንዶኔዢያ በአበባ ምርት በጋራ ለመስራት ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ኢንዶኔዢያ በአበባ ምርት በጋራ ለመስራት ተወያዩ፡፡

በቪዲዮ ኮንፍረንስ የተካሄደውን ውይይት ያዘጋጁት በጃካርታ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከኢንዶኔዢያ የአበባ ምርት አመቻች ማህበር ጋር ሲሆን በኢትዮጵያ ስላለው የዘርፉ ልማት ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

በውይይቱ በኢንዶኔዢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፕሮፌሰር አድማሱ ፀጋዬ፣ የወጪ ንግድ እና ቱሪዝም ልማት ጀነራል ዳይሬክተር አምባሳደር ረጋሳ ክፍሌ፣ የኢንዶኔዢያ የአበባ ምርት አመቻች ማህበር ሊቀመንበር ሉሲያ ራራስ እና ሌሌች የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ አበባ አምራቾችና ላኪዎች ማህበር ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ዘውዴ በኢትዮጵያ በዘርፉ ስላለው መልካም ዕድል ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የሁለቱ ሀገራት ኩባንያዎችም ልምዶቻቸውን አቅርበው በንግድ እና ትብብር በጋራ አብረው መስራት ስለሚገቧቸው ስራዎች ላይ መክረዋል፡፡

በውይይቱ ከሁለቱ ሀገራት የተውጣጡ 82 ኩባንያዎች መሳተፋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version