Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ባይደን ከፑቲን ጋር ኒውክሌርን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የአሜሪካው አዲሱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር ባደረጉት የመጀመሪያ የስልክ ውይይት ኒውክሌርን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡

ባይደን በውይይታቸው የሀገሪቱ የተቃዋሚ አመራር የሆኑት የአሌክሲ ናቫልኒይ ጉዳይም አንስተዋል፡፡

እንዲሁም የዩክሬን ጉዳይ፣ የሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ የምርጫ ጣልቃ ገብነት ሌሎች ጉዳዮች ማንሳታቸው ተሰምቷል፡፡

ፕሬዚዳንት ፑቲን የአሜሪካ አቻቸውን ምርጫውን በማሸነፋቸው “እንኳን ደስ አሎት” ማለታቸው ነው የተነገረው፡፡

ሁለቱ መሪዎች ካነሱዋቸው ዋነኛ ጉዳዮች መካከል የኒውክሌር ስምምነት ጉዳይ አንዱ ነው ተብሏል፡፡

በዚህም ሊጠናቀቅ ሳምንታት ቀርተውት የነበረውን የሁለቱን ሃገራት የኒውክሌር ስምምነት ለማራዘም መወሰናቸው ተገልጿል፡፡

ሀገራቱ በዓለም ላይ ከፍተኛ ኒውክሌር ከመታጠቃቸው አንጻር ጊዜውን ለማራዘም ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተስፋ ሰጪ ነው ተብሏል፡፡

በሌላ በኩል ባይደን ለፑቲን ለዘብተኛ ከነበሩት ከቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይልቅ ጠንካራ አቋም እንደሚያንጸባርቁ ይነገራል፡፡

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version