Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ በኦዲት ከ1ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የተጭበረበረ ገንዘብ ተገኘ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ በተደረገው የኦዲት ስራ ከ1ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የተጭበረበረ ገንዘብ መገኘቱ ተገለጸ።
የኦዲት ስራ የተሰራበት የገቢዎች ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የገቢ አሰባሰብ ባለሙያዎች ብቻ ከ1ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ እንዳጭበረበሩ ተመላክቷል።
ግብር ቀንሶ የማስቀረት ኃላፊነት ከተሰጣቸው ወደ መንግስት ቋት ያልገባ ከ52 ሺህ በላይ ብርም በኦዲት ተገኝቷል።
በዞኑ ፋይናንስ መምሪያ የኢንስፔክሽንና የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ሀብታሙ በቀለ÷ ባለሙያዎች የተሰበሰበውን ገንዘብ በደረሰኝ ላይ በሚያሳርፉበት ወቅት በሀጅና ቀሪ ደረሰኝ ላይ የተለያየ አድርጎ በመጻፍ እንዳጭበረበሩ በኦዲት ተረጋግጧል ብለዋል።
አንድ ባለሙያ ከ200 ሺህ ብር በላይ እንዳጭበረበረ ተደርሷልም ነው ያሉት።
እነዚህ ግለሰቦች በህግ ተጠያቂ መደረጋቸውን የጠቆሙት አቶ ሀብታሙ የተሸሸጉ እንዳሉም ተናግሯል።
አያይዘውም መሰል ችግሮች በሌሎች አካባቢዎች እንደሚኖሩ ማሳያዎች አሉ ብለዋል።
በዚህም መነሻነት በዞኑ ውስጥ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች የኦዲት ስራ እንደተጀመረ ጠቅሰዋል።
በታደሰ ተክሌ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version