አዲስ አበባ ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ6ኛው ሃገራዊ ምርጫ ሰላማዊ በሆነ መልኩ ያሸነፈ ሃሳብ ብቻ የህዝብ ውክልና ሊያገኝ እንደሚገባ ከፋና ቴሌቪዥን ጋር ቆይታ ያደረጉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተናገሩ ።
ከፋና ቴሌቪዥን ጋር ቆይታ ያደረጉ የአብን፣ የኢዜማና ትዴፓ ፓርቲዎች ያሏቸውን ፖሊሲዎችና ፕሮግራሞች ለህዝብ በማቅረብና በማስረዳት ሰላማዊ በሆነ መንገድ አሸናፊ የሆነ ሀሳብ ብቻ የህዝብ ውክልናን እንዲያገኝ የራሳቸውን ሚና እንደሚወጡ ገልፀዋል።
ነፃ ፍትሀዊና ሰላማዊ ምርጫ ማካሄድ ለዲሞክራሲ ስርዓትና ለሀገር ግንባታ ያለው ድርሻ ትልቅ መሆኑን ያነሱት ተፎካካሪ ፓርቲዎቹ ÷ ለዚህ ደግሞ የምርጫ ውጤቱ ብቻ ሳይሆን ሂደቱም ጭምር ነፃ ፍትሀዊና ሰላማዊ ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ለሙሉ ተግባራዊነቱም መንግስትና ተፎካካሪ ፓርቲዎችን ጨምሮ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ነው የገለፁት፡፡
በትዝታ ደሳለኝ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

