አዲስ አበባ ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬንያ ፕሬዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከኢፌዴሪ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ይ አህመድ የተላከ መልዕክት ዛሬ በቤተመንግስታቸው ተቀበሉ።
መልዕክቱን ለፕሬዚዳንት ኡሁሩ ያደረሱት የኤፌዴሪ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር እና የዶክተር አብይ ልዩ መልዕክተኛ አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ናቸው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የሚገኙበት ልዑክ ከኬንያ መንግስት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር ውይይት አድርገዋል።
አቶ ኃ/ማርያም እና ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ያደረጉት ውይይት በሁለትዮሽ፥ በአካባቢያዊ የሰላምና ፀጥታ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ነበር።
የኬንያው ፕሬዚዳንት ሁለቱ አገሮች ለአካባቢው ሰላም ቁልፍ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል።
የኢትዮ-ኬንያ ወዳጅነት እኛ የፈጠርነው ሳይሆን በትውልዶች ሽግግር እየጎለበተ የመጣ በመሆኑ የበለጠ ልናጠናክረው ይገባል ብለዋል።
በአቶ ኃ/ማርያም የተመራው ልዑክ በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲን በመጎብጀት ከዲፕሎማቶች ጋር መወያየታቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

