Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች በከተሞች ታጥረው የቆዩትን ልማቶች እና እሳቤዎችን ወደ ሌሎች አካባቢዎች የሚያሰፋ ነው- – አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች በከተሞች ታጥረው የቆዩትን ልማቶች እና እሳቤዎችን ወደ ሌሎች አካባቢዎች በማስፋት አዳዲስ የኢኮኖሚ አማራጮችን ለማስፋት ትልቅ ፋይዳ አለው አሉ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት በገበታ ለሀገር የገቢ ማሰባሰቢያ ብሄራዊ ኮሚቴ አባል እና የግሉ ዘርፍ አስተባባሪ፤ በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንግድ ዘርፍ ማስፋፊያ ሚኒስቴር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ፕሮጀክቶቹ ለአከባቢው ማህበረሰብ እና ከግሉ ዘርፍ ተጠቃሚነት አልፎም በሀገር ምጣኔ ሀብት ላይ ድርሻቸው የጎላ ይሆናል ብለዋል።

በተጨማሪም የፕሮጀክቶቹ መገንባት ለአብሮነታችን እና ሰላማችንም የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የግሉ ዘርፍ በግንባታው ሂደት ተሳትፎው ከተጠበቀው በላይ ሆኗል ብለዋል።

የሸገርን ፕሮጀክት የጥራት እና የፍጥነት ደረጃ የተመለከተው ሁሉ ነገን ብሩህ የማድረግ አቅም ያለውን ይህን ፕሮጀክት ለማገዝ እንዳላመነታም አነስተዋል።

በመጀመሪያ ደረጃ በተለያዩ የእራት ፕሮግራሞች ላይ የአምስት እና የአስር ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን፤መሰል የገቢ ማሰባሰቢያዎችን እስከ ታችኛው እርከን በማዉረድ ሁሉም እንዲሳተፍ እና ለሀገሩ የድርሻውን አንዲወጣ ይደረጋል ብለዋል።

አፈወርቅ አለሙ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

Exit mobile version