Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አምቦ ዩኒቨርሲቲ ከ5ሺህ በላይ ተማሪዎችን ያስመርቃል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አምቦ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 5ሺህ 73 ተማሪዎችን እንደሚያስመርቅ አስታወቀ።

የዩኒቨርሲቲው ሪጅስትራር ዳይሬክተር አቶ ማንደፍሮ ለገሰ ለኢዜአ እንደገለጹት ተመራቂዎቹ በመደበኛና ተከታታይ መረሃ ግብሮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።

ከተመራቂዎቹ መካከል 356 በሁለተኛ ዲግሪ፣ ስድስት በሶስተኛ ዲግሪ፣20 በህክምና ዶክተሬት እና ቀሪዎቹ በመጀመሪያ ዲግሪ የሰለጠኑ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው በሶስተኛ ዲግሪ (ፒ ኤች ዲ) የሚያስመረቃቸው ስድስቱ ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን አመልክተዋል።

ለትምህርት አሰጣጡ የሚያግዙና የኮሮና ወረርሸኝን ለመከላከል የጥንቃቄ እርምጃዎች ሲተገበሩ መቆየታቸውን ገልጸው፤ በአንድ ክፍል ከ30 ያልበለጡ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ መደረጉን አስረድተዋል።

በዚህም ዩኒቨርሲቲው ወረርሽኙን በመከላከል ያስተማራቸውን ከ5ሺህ በላይ ተማሪዎችን ጥር 22/2013 ዓ.ም ለማስመረቅ መዘጋጀቱን ነው የጠቀሱት።

ከተመራቂዎቹ መካከል 1 ሺህ 640 ሴቶች መሆናቸውም ተመልክቷል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version