አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የሴቶችን ተሳትፎ እና ውክልና ለማሳደግ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
የፓለቲካ ፓርቲዎች እና የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች እየተሳተፉበት የሚገኘው የውይይት መድረኩን የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ዴኤታ ሙና አህመድ በንግግር ከፍተውታል።
ሚኒስትር ዴኤታዋ በመጭው ምርጫ የሴቶችን ተሳትፎና ውክልና ማሳደግ እጅግ ወሳኝ መሆኑን አስምረውበታል።
ፓርቲዎች በምርጫው ምን ያክል እጩ ሴት ተመራጮችን ያቀርባሉ የሚለው እጅግ ወሳኙ ጥያቄ ነውም ብለዋል።
እስካሁን ተሳትፎን ለማሳደግ በለውጡ አመራር የተወሰዱ እርምጃዎች ትልልቅ ቢሆኑም አሁንም በሁሉም ደረጃ ተሳትፎና ውክልናን ይበልጡኑ ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።
በውይይት መድረኩ የሴቶች በውሳኔ ሰጭነትና ፓለቲካ ተሳትፎ ዙሪያ ያለው አጠቃላይ ሀገራዊ ሁኔታን አስመልክቶ የዳሰሳ ጥናት ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ነው።
ሴቶችን ወደ ውሳኔ ሰጭነት እንዳይመጡ ያደረጓቸው መዋቅራዊ፣ፓለቲካዊና ማህበራዊ ችግሮች ምን ምን ናቸው የሚሉ ጉዳዮችም በጥናቱ ተዳሰዋል።
በሀብታሙ ተ/ስላሴ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

