አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የብሄራዊ አስቸኳይ ጊዜ አስተባባሪ ማዕከል ዘርፈ ብዙ ምላሽ ሰጪ የሚኒስትሮች ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡
ኮሚቴው በትግራይ ክልል በህግ ማስከበር ሂደቱ ለተከሰቱ ሰብዓዊና ማህበራዊ ቀውሶች ምላሽ አሰጣጥ ተግባራትን እንዲሁም የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ የማቋቋም ሂደት ላይ ውይይት ያካሄደው፡፡
በሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትና ስርጭት እንዲሁም የመልሶ ማቋቋምሂደት ዙሪያ በየዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም የየዘርፍ ሪፖርት ቀርቧል።
በተጨማሪም የማዕከሉንና የየዘርፍ ባለድርሻ አካላትን የተግባር እንቅስቃሴ እንዲሁም የሰብዓዊ ድጋፍ እና እየተካሄደ ያለውን የመልሶ ማቋቋም ሂደት ከዕቅድ ጀምሮ አሁን ያለበትን ደረጃ የሚዳስስ ጽሁፍ ቀርቧል፡፡
በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ውይይት ተደርጎ የስርጭት አቅርቦትን ለማሳደግና የቅድሚያ የሚሰጣቸው ተግባራት መለየቱ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም አፋጣኝ ምላሽ መስጠቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የኮሚቴው ሰብሳቢ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል የቀጣይ ተግባራት መመሪያ መስጠታቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

