አዲስ አበባ ፣ ጥር 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብርር ሚኒስትር ሞሐመድ አብዲራዛቅን በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
አቶ ደመቀ ኢትዮጵና ሶማሊያ ጠንካራ ግንኙነት ያላቸው፣ በህዝቦች መካከልም ጠንካራ ትስስር ያላቸው ጎረቤታሞች አገሮች መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ኢትዮጵያ የሚቻለውን ሁሉ እንደሚታደርግ ቃል ገብተዋል።
በውይይታቸው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ፣ በኢትዮጵያ ሊደረግ በታቀደው ብሔራዊ ምርጫ፤ እንዲሁም በምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያ ለሚታካሂደው ምርጫ ዝግጅት መጀመሯን የጠቆሙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተመሳሳይ ምርጫ ለሚታደርገው ሶማሊያም የተሳካ ምርጫ እንዲሆን ተመኝተዋል።
ሞሐመድ አብዲራዛቅ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ለአገራቸው መረጋጋት ስታደርግ ለቆየችው አስተዋጽኦ አመስግነው፣ አገራቸው በቅርብ ጊዜ ለሚታደርገው ምርጫ ከክልል መግሥታት ጋር በንግግር ላይ እንደሚትገኝ ገልፀዋል።
አያይዘውም አገራቸው በሰሜን ኢትዮጵያ አጋጥሞ የነበረው ጉዳይ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን እንደምትረዳና ለዚህም ኢትዮጵያ የህግ የበላይነት ለማስከበር ያደረገችው ዘመቻ እንደምትደግፍ ተናግረዋል።
ምኒስትሩ አያይዘውም ሁለቱ አገሮች በምስራቅ አፍሪካ ሰላምና ትብብር እንዲጠናከር በጋራ ለሚያደርጉት ጥረት አገራቸው ቁርጠኛ መሆኗን ገልፀዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

