Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጃፓን ለዳሎታ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የማስፋፊያ ግንባታ ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ ፣ ጥር 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጃፓን በኦሮሚያ ክልል ገላን ከተማ ለሚገኘው የዳሎታ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የማስፋፊያ ግንባታ ድጋፍ አደረገች።
ለዚህ የማስፋፊያ ግንባታም የድጋፍ ስምምነት የፊርማ ስነ ስርዓት ተካሂዷል።
ስምምነቱን የገላን ከተማ ከንቲባ አህመድ እድሪስ እና በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ተፈራርመዋል፡፡
ለትምህርት ቤቱ የማስፋፊያ ግንባታም ጃፓን 89 ሺህ 944 ዶላር ለግሳለች፡፡
በድጋፉም አራት የማመሪያ ክፍሎች የያዘ ህንፃ ከተሟላ የመማሪያ ክፍል ቁሳቁስ እንዲሁም መፀዳጃ ቤትን በማካተት ይገነባል ተብሏል።
የገለን ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ውስጥ ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣውን የመዋለ ሕፃናት ትምህርት ፈላጊዎችን ለማስተናገድ የጃፓንን ድጋፍ የጠየቀ ሲሆን ÷የዚህ ፕሮጀክት ትግበራ ልጆቹ በትክክለኛው የመማሪያ አካባቢ እንዲማሩ ያስችላቸዋል ነው የተባለው፡፡
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version