አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2013 (ኤፍቢሲ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከ26ኛው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ፕሬዚዳንት አሎክ ሻርማ ጋር ተወያዩ፡፡
አቶ ደመቀ መኮንን የፕሬዚዳንቱን ጉብኝት ያደነቁ ሲሆን ከብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶሚኒክ ራብ ጋርም ባለፈው ሳምንት አየር ንብረትን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን አስታውሰዋል፡፡
አሎክ ሻርማ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ የሚከሰትን ተግዳሮት ለመከላከል እየሰራች ያለችው ተግባር አመርቂ እንደሆነና ይህም ለቀጠናው ሃገራት ተስፋ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የሚያተኩረው ጉባኤ በብሪታንያ አዘጋጅነት ይካሄዳል፡፡
አሎክ ሻርማ በጉባኤው ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ያሳየችው ቁርጠኛ አቋም ምሳሌ እንደሚሆንም ጠቅሰዋል፡፡
አቶ ደመቀ ኢትዮጵያና ጎረቤት ሃገራት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በጎርፍ፣ በድርቅ በተፈጥሮዋዊ አደጋዎች ተጠቂ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡
በአየር ንብረት ለውጥ የሚከሰተውን አደጋ ለመቀነስም ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ በመንደፍ ተግባራዊ እያደረገች እንደምትገኝ ማንሳታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በቀጣዮቹ አራት ዓመታትም በብሄራዊ ደረጃ ከ20 ቢሊየን በላይ ችግኝ ለመትከል መታቀዱንም ነው የጠቀሱት፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

