Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ታይዋንን ሉዓላዊ ሀገር ለማድረግ መሞከር የጦርነት ምክንያት ነው- ቻይና

አዲስ አበባ ፣ ጥር 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ታይዋንን ሉዓላዊ ሀገር ለማድረግ መሞከር የጦርነት ምክንያት ይሆናል ስትል ቻይና አስጠነቀቀች።

ይህ የቻይና ማስጠንቀቂያ የተሰማው ቻይና በአካባቢው የወታደራዊ እንቅስቃሴዋን ከፍ ካደረገች እና በታይዋን ደሴት አካባቢ የጦር አውሮፕላኖቿ በረራ ካደረጉ በኋላ ነው።

እንዲሁም አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለታይዋን ድጋፍ ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነት እና በኢስያ የሚኖራቸውን አቋም ከገለፁ በኋላ የመጣ አስተያየት መሆኑ ተነግሯል።

አሜሪካ ለቻይና መግለጫ በሰጠችው ምላሽ ከታይዋን ጋር ያለው መካረር ወደ ጦርነት ሊያመራ አይገባም ያለች ሲሆን የቻይናን መግለጫ አላስፈላጊ ስትል መግለጿን ቢቢሲ ዘግቧል።

ቻይና ዲሞክራሲያዊ የምትባለውን ታይዋንን ርቅት ላይ የምትገኝ አንዷ ግዛቴ ናት ስትል ታይዋን ግን ራሷን እንደ ሉዓላዊ ሀገር ትቆጥራለች።

ለታይዋን የነፃነት ሀይሎች መንገር የምንፈልገው ከእሳት ጋር የሚጫወት ራሱን ያቀጥላል ያለው የቻይና መከላከያ ሚኒስቴር የታይዋን ነፃነት ጦርነት ማለት ነው ብሏል።

Exit mobile version