Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የትራንስፖርት ዘርፉን በቴክኖሎጂ በመደገፍ የመንገዶችን መረጃ የሚያቀርብ የመረጃ ሶፍትዌር ስራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የትራንስፖርት ዘርፉን በቴክኖሎጂ በመደገፍ የመንገዶችን መረጃ የሚያቀርብ የመንገዶች ኔትዎርክ መረጃ ሶፍትዌር ስራ መጀመሩን የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ አስታወቁ።

በመንገድ ልማት ሪፎርም ማስፈጸሚያ ሰነዶችና በተጠናቀቁ የጥናት ውጤቶች ላይ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስን ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ውይይት ተካሂዷል።

በመድረኩ የዘርፉ መረጃዎች በቴክኖሎጂያዊ ዘዴ የሚቀርቡበት አሰራር እና የደረሰበት ውጤት ይፋ ሆኗል።

በዚህ ወቅት የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የትራንስፖርት ዘርፉን መረጃዎች በቴክኖሎጂ በተደገፉ ዘዴዎች ማቅረብ ለተመራማሪዎችና መረጃ ለሚፈልጉ በግልጽ ለማቅረብ ያስችላል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ይህንንም የሚያሳልጥ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመንገዶች መረጃን የሚያቀርብ የመንገዶች ኔትዎርክ መረጃ ሶፍትዌር ስራ መጀመሩን ሚኒስትሯ አስታውቀዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version