አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች ባለፈው ክረምት የተከሏቸውን ችግኞች የመንከባከብና ውሀ የማጠጣት መርሃ-ግብር አካሄዱ፡፡
በመርሀ ግብሩ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የኢነርጂ ባለስልጣን፣ የውሀ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት፣ የተፋሰስ ባለስልጣን፣ የውሃ ልማት ፈንድ ጽ/ቤትና ሉሎች የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ ተቋማት ተሳትፈዋል፡፡
የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች ባለፈው ክረምት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በኦሮሚያ ክልል ፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ልዩ ቦታው ደርባ ፊንጫ በሚባል አካባቢ የተከሏቸውን ችግኞች ውሃ አጠጥተዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

