Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የማይካድራ ጭፍጨፋ ሙሉ የምርመራ ውጤት ከሀኪሞች ሲገለፅ ይፋ ይደረጋል ተብሏል

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በማይካድራ ጭፍጨፋ ከተሳተፉት 279 ተጠርጣሪዎች መሀል ያልተያዙትን ለማደንና ለህግ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ገለፁ፡፡

ከማይካድራ ጭፍጨፋ ጋር በተያያዘ የአካባቢው ወጣቶች ሙሉ የምግብ አቅርቦት ተሟልቶላቸው ፀጥታን ታስከብራላችሁ በሚል ተመልምለው ስምሪት እንደተሰጣቸው ተገለፀ፡፡

ጭፍጨፉውን የሚያከናውኑበት ስለታማ ነገሮችም ቀድሞ ታድሏቸው እንደነበረ ተገልጿል።

በጉዳዩ ላይ በተደረገ ምርመራ ጭፍጨፋው ብሄር ተኮር እና በአብዛኛው ወንዶች ላይ ያተኮረ እንደነበር ተገልጿል፡፡

በሂደቱም 10 ሴቶች መደፈራቸው ነው የተነሳው።

ከጭፍጨፋው በኋላም በተለያዩ ቦታዎች ላይ ከ117 በላይ ጉድጓዶች መገኘታቸውን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የሙስናና የተደራጁ ወንጀል ጉዳዮች ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ፍቃዱ ፀጋ እና የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራልና የወንጀል ምርመራ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም መንግስቴ በጋራ በሰጡት መግለጫ አረጋግጠዋል፡፡

ሙሉ ውጤቱም በምርመራ ስራው ላይ ከተሳተፋ ሀኪሞች ሲገለፅ ይፋ እንደሚደረግ ተነግሯል ።

በማይካድራ ጭፍጨፋ ከተሳተፉ 279 ተጠርጣሪዎች ውስጥ 36ቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል፡፡

ቀሪዎቹ በስደተኛ ስም ወደ ሱዳን ገብተዋልም ነው የተባለው፡፡

ምርመራው አሁንም ያልተጠናቀቀና በተቋቋመው ግብረ ሀይል አማካኝነት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑም ተገልጿል ።

በትዝታ ደሳለኝ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version