አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የጅቡቲ ብሄራዊ ፖሊስ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የስራ ጉብኝት አደረጉ።
የጅቡቲ ብሄራዊ ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር ኮሎኔል አብዱላሂ አብዲ ፋራህ እና የጅቡቲ ብሄራዊ ፖሊስ የመረጃ ደህንነትና ኢምግሬሽን ሀላፊ ኮሎኔል አብዱልቃድር ኢብራሂም በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲን ሠንዳፋ በመኘት ጎብኝተዋል።
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ም/ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ ፣ ምክትል ፕሬዚዳንቶች እና ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ጉብኝት አድርገዋል፡፡
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሸን እንዳስታወቀው ቡድኑ በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙትን ቤተ-መፅሀፍት፣ ቤተ-መዘክር እንዲሁም አዲስ የተገነባውን የዩኒቨርሲቲውን ግቢ ጎብኝተዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

