Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኤጀንሲው እናቶች ከወሊድ በኋላ ለሚከሰት የደም መፍሰስ አስፈላጊውን ህክምና እስኪያገኙ የመጀመሪያ እርዳታ ለማድረግ የሚያገለግል የህክምና መገልገያ እያሰራጨ እንደሆነ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ እናቶች ከወሊድ በኋላ ለሚከሰት የደም መፍሰስ አስፈላጊውን ህክምና እስኪያገኙ ድረስ የመጀመሪያ እርዳታ ለማድረግ የሚያገለግል የህክምና መገልገያ እያሰራጨ እንደሆነ ገለጸ፡፡

የህክምና መገልገያው ለአፋር፣ አማራ፣ቤንሻንጉ ጉሙዝ ፣ጋምቤላ ፣ሀረሪ ፣ኦሮሚያ ፣ሲዳማ ፣ ሶማሌ፣ድሬደዋ ፣ደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል፣ ድሬደዋና ለአዲስ አበባ ከተማ ከተማ አስተዳደር እንደሚሰራጭ የስርጭት ቡድን መሪ አቶ ተስፋሁን አብሬ ተናግረዋል፡፡

በድሬደዋ ፣ባህር ዳር ፣ጋምቤላ ፣ አሶሳ ፣ ሰመራ ፣ ሐዋሳ ፣ ጅጅጋና በአዲስ አበባ ቁጥር 1 ቅርንጫፎች አማካኝነት ስርጭቱ እንደሚካሄድም አስታውቀዋል።

የህክምና መገልገያው እናቶች ከወሊድ በኋላ ለሚከሰት የደም መፍሰስ አስፈላጊውን ህክምና እስኪያገኙ ድረስ የመጀመሪያ እርዳታ ለማድረግ የሚያገለግል ነው።

ኤጀንሲው ከጥር 18 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ መገልገያውን እያሰራጨ ሲሆን 12 ሚሊዮን 829 ሺ 201 ብር ወጪ እንደተደረገባቸው ቡድን መሪው አብራርተዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version