Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን አስመረቁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን አስመርቀዋል፡፡

የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሀግብሮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 59 ተማሪዎቹን ለመጀመሪያ ጊዜ አስመርቋል፡፡

የደብረ ታቦር ዩንቨርሲቲም በ39 ትምህርት ክፍሎች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 518 ተማሪዎችን ለ7ኛ ጊዜ አስመርቋል፡፡

የ7ኛ ዙር ተመራቂዎችም በመጀመሪያ ዲግሪ 2 ሺህ 486 እንዲሁም በሁለተኛ ዲግሪ 32 ተማሪዎች እንደሆኑ ተነግሯል፡፡

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲም እንዲሁ ለመጀመሪያ ጊዜ 827 ተማሪዎቹን አስመርቋል።

አምቦ ዩኒቨርሲቲ በ4 ካምፓሶቹ በተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ያሰለጠናቸውን 5615 ተማሪዎቹን በዛሬው እለት አስመርቋል ።

የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ እና በተከታታይ መርሐ ግብር መጀመሪያ ዲግሪ ወንድ 1 ሺህ 52፣ ሴት 229 በድምሩ 1 ሺህ281፣ በሁለተኛ ዲግሪ ወንድ 373፣ ሴት 86 በድምሩ 459 እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ በሦስተኛ ዲግሪ 1 ተማሪ በድምሩ 1 ሺህ 741 ተማሪዎቹን አስመርቋል፡፡

የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲም በተለያዩ መርሀግብሮች ሲያሰለጥናቸው የነበሩ 4 ሺህ 192 ተማሪዎቹን አስመርቋል፡፡

በተመሳሳይ መቱ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ማስመረቁም ነው የተገለጸው፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version