አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በሀረሪ ክልል በተለምዶ የድሃ ቤት ተብሎ የሚጠራው ፕሮጀክት ተጠናቆ በዛሬው እለት ተመረቀ።
በክልሉ በተለምዶ የድሃ ቤት ተብሎ የሚጠራው የበርካታ አቅመ ደካማ ወገኖች የጋራ መኖሪያ ቤት በ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ወጪ እድሳት ተደርጎለት በዛሬው እለት ተመርቋል።
ይህ የጋራ መኖሪያ እድሳቱ ሳይደረግለት በፊት ለመፍረስ የተቃረበ እና ጣሪያውም ተነቃቅሎ ያፈስ የነበረ ቤት መሆኑን ከሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ፕሮጀክቱን መርቀው የከፈቱት የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ እንዳሉት በቀጣይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ዜጎች ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት ይሰራል።
ከዚህ ቀደም የደሃ ቤት ተብሎ ይጠራ የነበረው ቤት ከእድሳት በኋላ የሰላምና ፍቅር የጋራ መኖሪያ ቤት ተብሎ መሰየሙን የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ቤት ለሚኖሩ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር እንደሚሰራ ገልፀዋል።
በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ እና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላን ጨምሮ የክልሉ ካቢኔ አባላትና ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

